Fitawrary Primary and middle School
Announcement Announcement

Announcement

01st February, 2025

 ምክር ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅን አጸደቀ፡፡ (ጥር 22/2017 ዓ.ም) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባው የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅን አጽድቋል፡፡ የአዋጁን ረቂቅ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) አቅርበዋል፡፡ አዋጁ ትምህርትን በእኩልነት እና ፍትሃዊነት በመላ ሀገሪቷ ተደራሽ ለማድረግ የጎላ ሚና እንዳለው አብራርተዋል፡፡ እንዲሁም፣ አዋጁ የመምህራንን ጥራት እና ጥቅም የሚያስጠብቅ፣ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና የትምህርት አስተዳደሩን ብቃት ለማረጋገጥ ድርሻው ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም የአስተማሪነት ሙያ እንዲከበር እና በሂደትም የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ለመስጠት ከፍተኛ ሚና እንዳለው መገለጹን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 1368/2017 ሆኖ በሁለት ተቃውሞ፣ በአሥር ድምጸ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

.

Copyright © All rights reserved.

Created with